Biography

የተቋሙ መስራችና ዳይሬክተር አጭር ታሪክ

ሀገር ቤት ሀላፊነቱ የተወሰነ የመዝናኛ ድርጅት መስራችና ዳይሬክተር ይበልጣል ታደሰ ከልካይ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ አበባ ኮከብ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ የግል ትምህርት ቤት ተከታትሎ በመቀጠልም ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ቤት በቴአትር ጥበባት የመጀመርያ ዲግሪውን በ2009ዓም በማግኘት በማዕረግ ተመርቋል፡፡ ገና የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለ ከተማው ላይ ባሉ የፊልም ትምህርት ቤቶች ውስጥ በመሄድ ጎን ለጎን የማታ አጫጭር ኮርሶችን ለተማሪዎች ስልጠና ይሰጥ ነበር፡፡ከልጅነቱ ጀምሮ በቤተክርስትያን ውስጥ የጥበብ እንቅስቃሴ በማድረግና ግጥም በመፃፍ የስነ-ፅሁፍ ክህሎቱን ማሻሻል ችሏል፡፡ በ2007 ዓም ‹‹ አትቅና አትበይኝ ›› የተሰኘ 76 የግጥም ስብስብ ያለበትን የግጥም መድብል ለንባብ አብቅቷል፡፡ በ2006ዓም በረዳት አዘጋጅነት ‹‹ ህመሜ ›› የተሰኘ ፊውቸር ፊልም አዘጋጅቶ ለዕይታ ያበቃ ሲሆን በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩ 32 ሲኒማ ቤቶች ውስጥ የታየ ሲሆን በዩቲዩብም ከ1.3 ሚሊየን በላይ ተመልካቾች ተመልክተውታል፡፡ በ2008ዓም ‹‹ በጊዜ ›› የተሰኘ ፊውቸር ፊልም በፕሮዳክሽን ኮርዲኔተር እና በዝግጅት ሰርቷል፡፡ ይበልጣል ታደሰ በአሜሪካን ሀገር በሚገኘው Hollywood and African prestigious Award ላይ በምርጥ ፊልም አዘጋጅ ለእጩነት ቀርቦ ምርጥ አምስት ውስጥ ለመግባት በቅቷል፡፡ በ2009ዓም ‹‹ ይዳኘን ያየ ››የተሰኘ ፊውቸር ፊልም በፕሮዳክሽን ማናጀር እና ዝግጅት ከሰራባቸው ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የጥበብ ምሽቶችን በማዘጋጀት ከ100 በላይ ተዋንያን የሚሳተፉባቸውን ሙዚቃዊ ተውኔቶች ፅፎ በማዘጋጀት በበርካታ ቦታዎች በተለይ ከሴቶች ጋር የተያያዘ ስራ በ UNDP (united Nation developing program)  ጨምሮ ስራዎቹን ለማቅረብ በቅቷል፡፡ በሚራክል ፊልም ትምህርት ቤት ውስጥ ከ1500 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትወናና የድርሰት አፃፃፍ አጫጭር ኮርሶችን ለተከታታይ ሶስት አመታት ሰጥቷል፡፡ አሁን ኑሮውን በአሜሪካን ሀገር በማድረግና የራሱን ድርጅት በመክፈት በመዝናኛው ዘርፍ በጎ ተፅዕኖ ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል፡፡

Who’s Yebeltal T kelkay

The founder and director of Hager bet entertainment llc, yebeltal Tadesse Kelkay attended primary and secondary school in Addis Ababa kokeb primary and secondary private school, then joined Addis Ababa University and graduated from Addis Ababa University school of Theatre Arts with distinction in 2009. While he was still a University student. He used to go to film schools in the city and give training to students in short evening courses. In 2007, he completed and published a collection of 76 poems called << Atekena Atbyigne >> . In 2006, As an assistant producer, he produced and released a future movie called  << Hmeme >>   which was shown in 32 cinemas in Ethiopia at the time and was watched by more than 1.3 million viewers on YouTube. In 2008, He worked as a production coordinator and producer for a future movie called << begize>>  Also he nominated by best director at Hollywood and African prestigious Award in the united states of America. A future film called << Yidagnen yaye >> also produced by yebeltal Tadesse. He has organized several poetic nights in Addis Ababa city, Written and produced several musical plays in which more than 100 actors participate, and presented his works in many places, especially work related to women and children , including UNDP ( United Nation Developing Program). He has given short courses in acting and essay writing to more than 1500 students at Miracle Film School for Three consecutive years. Now he is making a living in America and opening his own company to make a positive impact in the entertainment sector.